ዱባ ፣ ጎመን እና ካሮት

ተረት ተረት — የላም በረት አንድ ሰውዩ ነበረ፡፡ እሺ! ከቤቱ ጀርባ ትልቅ ቦታ ነበረው፡፡ ከለታት አንድ ቀን በትርፍ ጊዜዮ ለምን አትክልት ተክዮ ሲደርስ አልመገብም ብሎ ዱባ ፣ ጎመን እና ካሮት የአትክልት ቦታ አዘጋጅቶ ተከለ፡፡ እሺ! ከዛ ጎመን ፣ ዲባ እና ካሮት ሁሉም ማደግ ጀመሩ፡፡ አድገው አድገው አድገው … ትልቅ ሲሆኑ ጎመን እና ዱባን እንዲህ አለችው፡፡ እሺ! እኔ አድጌ ቅጠሌ ትልቅ ሆኖ ጌታዮ ቀቅሎ ይበላኛል፤ አንተም በጥም ትልቅ ፍሬ አፍርተሃል፡፡ ይህ ፊታችን ተደንቅሮ ፍሬ የሌለው ካሮት ምን ይሰራል፡፡ ቦታ ከሚያጣብ ለጌታችን እንዲነቅለው ለምን አንነግረውም ተባባሉ፡፡ ከዛ ሰውዮው ሲመጣ ይህንን ነገሩት፡፡ ሰውዮውም በአስተሳሰባቸው ተገርሞ … ካሮት እኮ እንደናንተ የሚታይ ፍሬ ባይኖረውም ወደ መሬት ውስጥ የሚያድግ የማይታይ በጣም ጣፋጭ የሆነ ጠቃሚ ምግብ ነው ብሎ አስረዳቸው፡፡ እነርሱም በጣም ተገርመው ለካ ብዙ የማይታይ ጥሩ ጥሩ ፍሬ ያላቸው ነገሮች አሉ ብለው ካሮትን ይቅርታ ጠየቁት፡፡ ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ፡፡ ልጆች ከዚህ ተረት፡፡ ሁሉም ልጆች ብዙ የተደበቀ እኛ የማናየው ጥበብ ፣ ጉብዝና ሊኖራቸው እንደሚችል ተማርን፡፡ መልካም ስለዚህ እናንተም ሁሉም ጋደኞቻችሁን ውደዱ፡፡

እንቆቅልዕ — ምን አውቅልህ እንቆቅልሽ — ምን አውቅልህ

ጥቁር አዞ ተጠማዞ

እንቆቅልዕ — ምን አውቅልሽ እንቆቅልሽ — ምን አውቅልሽ

ጸጉሯን አበጥራ ገበያ የምትወጣ

መልሶቻችሁን ኮሜንት በማረጊያው ላይ ስማችሁን ገልጻችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ